ህግ እና ደንብ አንቀጽ 1 የሰ/ት/ቤቱ ስያሜ እና ባሕሪ 1.1 የሰ/ት/ቤቱ ስያሜና ባህሪ በአጠቃላይ ሰ/ት/ቤት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህ ደንብ ባለበት ሀገርና አጥቢያ ቤተክርስቲያን ስም የፊላደልፊያ ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን አንቀፀ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት እየተባለ ይጠራል፡፡ የተቋቋመበት አላማ በቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ ዓዋዲ) መሠረት ሲሆን ወጣቶችን እና...
More
ህግ እና ደንብ አንቀጽ 1 የሰ/ት/ቤቱ ስያሜ እና ባሕሪ 1.1 የሰ/ት/ቤቱ ስያሜና ባህሪ በአጠቃላይ ሰ/ት/ቤት ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህ ደንብ ባለበት ሀገርና አጥቢያ ቤተክርስቲያን ስም የፊላደልፊያ ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን አንቀፀ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት እየተባለ ይጠራል፡፡ የተቋቋመበት አላማ በቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ ዓዋዲ) መሠረት ሲሆን ወጣቶችን እና ሕፃናትን በክርስቲያናዊ ህይወት ለማነጽ ነው፡፡ አንቀጽ 2 ራዕይ እና ተልዕኮ 2.1ራዕይ፡- በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ሕፃናት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እምነት እና ሥርዓት የሚሄዱ ሆነው በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እንዲሁም በክህነታቸው ሲያገለግሉ እና በዓላማዊው በአስኳላው ትምህርታቸው ውጤታማ ሆነው ማየት። 2.2 ተልዕኮ፡- 2.2.1 በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ሕፃናትን ትክክለኛውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ትምህርተ ሃይማኖት እና የአብነት ትምህርት በማስተማር የቤተክርስቲያኗን ዶግማ፣ሥርዓት፣ትውፊት፣ታሪክ እና ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያውቁ ማድረግ፣ 2.2.2 የተለያዩ እምነት መሰል ድርጅቶች በሚያደርጉት አባላት እንቅስቃሴ እንዳይነጠቁ አስፈላጊውን ሁሉ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ 2.2.3 የተለያዩ መንፈሳዊ ጉባዔዎችን እና ጉዞዎችን በማጋጀት ለምዕመኑ ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር፣ 2.2.4 ለአባላት እና ለአጥቢያው ምዕመናን የበጎ አድራጐት ሥራዎችን መስራት እና የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፡፡ አንቀጽ 3 አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ 3.1 የኢትዮጵያ፣ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ የሆነ/ች/ 3.2 በሰ/ት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ ለመመራት ፈቃደኛ የሆነ/ች/ 3.3 ዕድሜው/ዋ/ ከ 4 ዓመት በላይ የሆነ 3.4 በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጠውን የቀዳማይ ተከታታይ
Less