ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 1 ቁጥር - ጥር ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት JANUARY 2012 ezralit@gmail.com ጤና ይስጥልኝ፤ ፈረንጅኛውን ለምትቆጥሩ መልካም አዲስ ዓመትና ፍሬያማ 2012 እመኝላችኋለሁ። እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን። በዚህ የዕዝራ ስርጭት ፕሮቴስታንታዊ ጅሃድ በሚል...
More
ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 1 ቁጥር - ጥር ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት JANUARY 2012 ezralit@gmail.com ጤና ይስጥልኝ፤ ፈረንጅኛውን ለምትቆጥሩ መልካም አዲስ ዓመትና ፍሬያማ 2012 እመኝላችኋለሁ። እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን። በዚህ የዕዝራ ስርጭት ፕሮቴስታንታዊ ጅሃድ በሚል ርእስ የተዘጋጀና የተሰራጨ ዲቪዲ ነበረ። በYouTube ላይም የዲቪዲው አጫጭር ቁራጮች በተለያዩ ምንጮች ተኮልኩለዋል። ዲቪዲው በፓስተር ዳዊት ስብከት ላይ የተሰጠ ምላሽ ቢሆንም በነገረ ማርያም ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መጣጥፍ በ3 ክፍል የተሠራው ክፍል አንድ ሆኖ የመልሱ ምላሽ ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ማርያም በእርግጥ ማን መሆኗን የሚያመለክት ነው። የተፈጠሩ ተረቶችን ሳይሆን ቃሉን ነው ማንበብና መቀበል ያለብን። ጌታ ቢፈቅድና ብንኖርም በሁለተኛውም ይኸው ይቀጥልና በመጨረሻው ደግሞ ተአምረ ማርያም የተሰኘውን መጽሐፍ በጥቂቱ እንቃኛለን። በሁለተኛው እንደሚገባ ኑሩ በሚል የጳውሎስን መልእክት ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ጥናት እንቀጥላለን። የተጠራንበትና መዳናችን የታወጀልን ወንጌል የከበረ ወንጌል ነው፤ ታዲያ የዚያኑ ያህል የእኛም ኑሮ ያንን ያንጸባረቀ መሆን ይገባዋል። የተገባው ነውና እንደሚገባ ልንኖር ተጠርተናል። በሦስተኛው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ በሚል ርእስ ስለ ጌታችን ልደተ ሥጋ በማገለግልባት ቤተ ክርስቲያን በዚህ የልደት ሰሞን ያካፈልኩትን ለጽሑፍ እንዲመች አድርጌ አቅርቤዋለሁ። መልካም ንባብ። ዕዝራ ስነ ጽሑፍ፥ ዘላለም መንግሥቱ
Less