1 ቁጥር ፳፭ -ግንቦት ፪ሺህ ፮ ዓመተ ምሕረት MAY 2014 ሰላምና ጤና ይብዛላችሁ፤ በዚህ ስርጭት ሦስት አጫጭር መጣጥፎች አቅርቤአለሁ። የተጀመሩት ተከታታይ ጽሑፎች በተከታዩ ስርጭት ይቀጥላሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ባለፉት 11 ዓመታት እየሠራሁ ስላለሁትና የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት እንዲያልቅ ለምመኘው ሥራ ጸሎትን የሚጠይቅና በአጭር የሚያስተዋውቅ ነው። ቀዳማዊ የአማርኛ መጽሐፍ...
More
1 ቁጥር ፳፭ -ግንቦት ፪ሺህ ፮ ዓመተ ምሕረት MAY 2014 ሰላምና ጤና ይብዛላችሁ፤ በዚህ ስርጭት ሦስት አጫጭር መጣጥፎች አቅርቤአለሁ። የተጀመሩት ተከታታይ ጽሑፎች በተከታዩ ስርጭት ይቀጥላሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ባለፉት 11 ዓመታት እየሠራሁ ስላለሁትና የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት እንዲያልቅ ለምመኘው ሥራ ጸሎትን የሚጠይቅና በአጭር የሚያስተዋውቅ ነው። ቀዳማዊ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስን በመጽሐፍ መልክ ማንበብ ብቻ ሳይሆን በኮምፒዩተር፥ በእጅ ስልካችን፥ ስንፈልግ እናነብበዋለን፥ ሲያሻን እንሰማዋለን፥ ቆርጠን ለጥፈን እንልከዋለን። ስለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እግዚአብሔር ይመስገን። ቃሉ ግን በቋንቋችን በቀላሉ የተገኘ አይምሰለን። ዛሬ በብዙዎቻችን እጅ ስላሉት ሳይሆን ከነዚህ ቀድሞ ስለተተረጎመውና የተሰራጨው ስለ መጀመሪያው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉምና በሰፊውም ባይሆን እንመለከታለን። የተሰቀለው ክርስቶስ ክርስቶስን መስበክ ድንቅ ነው። ግን የቱ ክርስቶስ? ያልተሰቀለውን ኢየሱስ የሚሰብኩ እንዳሉ እናውቃለን? ጌታና አምላክ የሆነውን ክርስቶስ ሰውና ነቢይ ብቻ ነው። የተሰቀለው ኢየሱስ ሳይሆን እርሱን የሚመስል ሌላ ነው ለሚሉ መልስ አለን? የክርስቶስ መሰቀል፥ መሞትና መነሣት የተረጋገጠ እውነት ነው። የጳውሎስ የስብከቱ ማዕከል የተሰቀለው ክርስቶስ መሆኑ በመስቀሉ የተፈጸመውን ቤዛነት ለማጉላት ነው። መልካም ንባብ። ዘላለም መንግሥቱ / ዕዝራ ስነ ጽሑፍ። የዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት ግብና ዓላማ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትና ይዘት ያላቸውን ቅዱሳንን የሚመግቡ ከአጫጭር መጣጥፎች እስከ ትልልቅ የማስተማሪያ መርጃዎች በማዘጋጀት ቤተ ክርስቲያንን መደገፍና በዚህም እግዚአብሔርን ማክበር ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ቀዳማዊ የ
Less